በመመሪያና ደንብ ዝግጅት ወቅት ያልተጣረዘ ስራን ለመከወን የፌዴራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅን ማወቅ እንደሚገባ ተገለፀ።

ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ መጋቢት 18 ቀን 2016ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በአስፈፃሚ ተቋማት ለሚገኙ ዳይሬክተሮች የፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ የሁለተኛውን ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘመናይ ሸገና እንደገለፁት የስልጠናው ዋና አላማ በመመሪያና ደንብ ዝግጅት ወቅት ያልተጣረዘ ስራን ለመከወን የፌዴራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅን ጠንቅቆ በማወቅ እና ግንዛቤ በመጨበጥ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ጠቅሰው ሰልጣኞች ስልጠናውን በተገቢው በመከታተል አስፈላጊውን እውቀት በመያዝ ወደስራ መግባት ይገባል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

የስልጠናው ዋና ዋና ይዘቶች ስለ አስተዳደር ህግ ምንነት ፣የአስተዳደር ስነ -ስርዓት ህጎች ፣ የአዋጁ አላማዎች፣ የአዋጁ ተፈፃሚነት ወሰን፣ በመመሪያ አወጣጥ ሂደት የሚስተዋሉ ችግሮች፣ አዋጁ ያመጣቸው መፍትሔዎች ፣መመሪያ የሚወጣባቸው ጊዜዎች ስልጠናው እነዚህን ትኩረት በማድረግ እየተሰጠ ይገኛል።