በተቋማት ያለውን የአገልግሉት አሰጣጥ ስርዓት ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ግልፅ በማድረግ ብልሹ አሰራሮችን በጋራ በመዋጋት ተፈላጊውን የአገልግሎት ጥራት ማረጋገጥ እንደሚቻል ተገለፀ፡፡

ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፣ መጋቢት 17 ቀን 2016

የአዲስ አበባ ከተማአስተዳደር ፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማ ቢሮ በተቋማት የተካሄደው ሪፎርም ከበጀት ዓመቱ አስቀድሞ በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመተት ውስጥ በክትትልና ድጋፍ፣ በሱፐርቪዥን፣ ውጤቶች እና በየዚዜው በተደረጉ ጥናቶች መሰረት በማድረግ በከተማ አስተዳደሩ ላይ ያሉ ተቋማት በሚሰጧቸው አገልግሎቾች ጥራት መሰረት ያደረገ ለማድረግ ያሉ ክፍተቶችና ጠንካ ጎኞችን በመለየት እንዲሁም አጠቃላይ በካቢኔ ግምገማ በልየታ የተገኙ ተቋማትን በመለየት የህብረተሰብን ቅሬታ ለመፍታትና እንግልትን ለመቀነስ ብሎም የተረጋገጠ የአገልሎት አሰጣጥ ጥራት ለማምጣት ያለመ የሪፎርም ስራ ወደ ተግባር እንደገባ መደረጉን ተገልጿል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ወደ ሪፎርም ስራው ለመግባት 5 ዋና ዋና መሰረታዊ ጉዳዮችን መፈተሻቸው የተገለፀ ሲሆን እነዚህም የአደረጃጀት ማሻሻያ በማድረግ የስልጣንና የሃላፊነት መደበላለቆችን በመለየት ግልፅ አደረጃጀቶችን ለመስራት፣ የአሰራር ማሻሻያ በማድረግ ለአገልግሎት አሰራት እንቅፋት የሚሆኑ አዋጆች መመሪያዎች እና ደንቦችን በመፈተሸ ማሻሻያ ለማድረግ፣ የሰው ሀይል ስምሪት በመለየት የተገልጋይ የመገልገል ፍላጎትን የሚሞላ የሰው ሀይል ለማሰማራት፣ ቴክቦሎጂን በመጠቀም ጥራት ያለው አገልግሎትለመስጠት እና ምቹ የስራ ከባቢን ለተገልጋዩና ለሰራተኛው ለመፍጠር አኳያ ላይ ተቋማት ያሉባቸውን ክፍተቶችን አጥንተው እንዲያቀርቡ በማድረግ ወደ ሪፎርም እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል፡፡

በ16ቱ ተቋማት የሪፎርም ስራ በመጀመር 19ሺ የሚጠጉ ሰራተኞች የቴክኒክና የባህሪ ፈተና በገለልተኛ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲወስዱ መደረጉ የተገለፀ ሲሆን በዚህ መሰረት አጠቃላይ ሰራተኛው ወደ ድልድል በማስገባት ምደባ እንዲያገኙ በማድረግ በምደባው ወቅት ያሉ ቅሬታዎች በየደረጃው እንዲታዩና በድልድል ደንቡ መሰረት ትክክለኛውን የሰው ሀይል በትክክለኛው ቦታ የመመደብ ስራው እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል አገልግሎት ሰጪው በብልሹ አሰራር የተያዘ በመሆኑ ተገቢውን አገልግሎት በተገቢው ሰዓት ለማግኘት ከለመቻልም ባለፈ የቅሬታ አቀራረብ ዘዴዎች ለብልሹ አሰራሮች እንዱንጋለጥ አስገድደውናል ሲሉ በቀጥታ የስልክ መስመር አድማጮች ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡

በተያያዘም አገልግሎት ፈላጊው ወደ ተቋማት በሚመጣበት ወቅት አገልግሎት ሰጪው የሚጠበቅበትን አገልግሎት ለመስጠት መቸገር እንደሚታይ ገልፀው ቢሮው የሚያደርገው ክትትል እስከምን ድረስ ነው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለተነሱ ጥያቆዎች ምሳሾችን የሰጡት የቢሮው የሪፎርም ዳይሬክተር አቶ አዴና ተበጀ እና የሰው ሀብት ኦዲት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን በሰጡት ምላሽ በተቋማት ያለው አሰራራቸውንና አገልግሎታቸውን ለተገልጋይ ግልፅ ያለማድረግ ችግሮች በመኖራቸው ለብልሹ አሰራር ተገልጋዩን ያጋልጡ የነበሩ መሆናቸውን ጠቅሰው በተጀመረው የሪፎርም ስራ ተቋማት አሰራሮቻቸውን በመፈተሸና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀላል ለማድረግ በማለም የተጀመረ ስራ መሆኑ አስረድተዋል፡፡

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚፈለገውን አገልግሎት ከመስጠት አንፃር የተቋማት አገልግሎትን መመዘኛ ስታንዳርድ በማዘጋጀት ክትትል የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እየቀጠለ እንደሚገኝ ገልፀው የሰራተኛውን የመፈፀም ብቃት ጉዳይ በማጤን የስነምግባርና የአተገባበር ጉድለቶችን ለመቅረፍ እየተሰራም እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

ይህ የተባለው ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔቶርክ ጋር በመተባበር በሚያቀርበው የቀጥታ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ነው።