ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ መጋቢት 13 ቀን 2016ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በሀገራችን ደረጃ ለ48ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአለም የሴቶች ቀን አስመልክቶ በዓሉ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ በማረጋገጥ ለሀገር ሰላምና ልማት ለማምጥት በማለም የሴቶችን ተጠቃሚነት ሚያረጋግጥ ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ በሚል መሪ ቃ የአለም የሴቶች ቀንን ከአጠቃላይ ሰራተኛው ጋር አክብሯል፡፡
በእለቱም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በቢሮው የማስፈፀም አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ፍቅርተ አበራ እንደተናገሩት የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ የሴቶችን ቀን የምናከብረው ሴቶች እኩልነትን ከማስከበር አንፃር ያደረጓቸውን ተጋድሎዎችንም እንደሰሩ በማስታወስ ጭምር መሆኑን ገልፀዋል።
የሴቶችን ተሳትፎ በማጠናከር ሰላምና ልማታችን ማረጋገጥ እንደሚቻል እና ሴቶች ያሉባቸውን ማህበራዊ ተጠያቂነት በብቃት የሚወጡና ለተቋማት ብሎም ለሀገር መሰረት መሆናቸው የሚታወቅ እንደሆነ ጭምር ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸውን በማሳደግ ሀገር የጀመረችውን እድገት የሚያስቀጥሉ ጠንካራ ሴቶችን መፍጠር እንደሚቻል ገልፀው የሰው መሰረት የሚጣለው በእናቶች እንደመሆኑ መጠን ሀገር የእናት ተምሳሌት በመሆኗ ሴቶችን በአቅም መገንባት ሀገር በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት በመሆኑ ሴቶችን በሁለንተናዊ መሰረት መገንባት ይገባናል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
አክለውም በተቋማትና በሀገር ደረጃ የሚከበረው የማርች 8ቀን ሴቶችን እናብቃ ሰላምና ለማትን እናረጋግጥ የሚለው መፈክር ከቃላት ባሻገር በተጨባጭ በመሰራት እርስ በርስ በመደጋገፍና በጋራ በመሆን ከሚታየው በላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተናግረው በቀጣይም ወደ ሰራ የምንገባበት እንጂ ለአንድ ቀን ብቻ ተከብሮ የሚቀር አይደለም ሲሉ ጠቁመዋል።
ሰነዱን ያቀረቡት የቢሮው ፎካል ፐርሰን የሆኑት ወ/ሮ አቦነሽ አስፋው የሴቶችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሰረት የጣለው የሴቶች ቀን ንቅናቄ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው ያሉ ሲሆን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ ዳራ የሴቶች ቀን መከበር ፋይዳ፣ የሴቶች ቀን ከኢትዮጵያ ታሪክ አንጻር እና በሴቶች መብት ላይ በሰፊው በሰነዱ ቀርቧል ።