Skip to content 
Location
Arada Subcity, woreda 06 Addis Ababa, Ethiopia
Date
ማክሰኞ, 12 ጥር 2018 4:22 ጥዋት
Last updated
January 20, 2026 04:22
Weather
Addis Ababa 🌦 +14°C
ማስታወቂያዎች

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

06 ጥር 2018

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለአዲስ መሶብ ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ባሉት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

በመሆኑም ፍላጎት ያላችሁ ስራ ፈላጊዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከጥር 5/2018ዓ.ም  ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኦንላይን ብቻ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እና ማሳሰቢያዎች፦

  • የምዝገባ ሁኔታ፦ ምዝገባ የሚከናወነው በኦንላይን (በድረ-ገጽ) ብቻ ነው። በአካል በመቅረብ መመዝገብ አይፈቀድም።

  • ብሔራዊ መታወቂያ፦ ባለ 16 አሃዝ ዲጂታል የናሽናል አይዲ ቁጥር (FAN / FCN) መኖር ግዴታ ነው።

  • የምረቃ ዘመን፦2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁ መሆን አለባቸው።

  • ለዲግሪ ተመራቂዎች፦ የብሔራዊ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ማለፊያ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  • የውጤት ገደብ (GPA)፦ * ለወንዶች፦ 3.5 እና ከዚያ በላይ

    • ለሴቶች፦ 3.0 እና ከዚያ በላይ

  • ለዲፕሎማ ተመራቂዎች፦ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው።

እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ከታች ያለውን የድረ-ገጽ ሊንክ በመጫን መመዝገብ ይችላሉ፦ 👉 https://www.aacapsjobs.gov.et