Skip to content 
Location
Arada Subcity, woreda 06 Addis Ababa, Ethiopia
Date
ሐሙስ, 08 ሚያዝያ 2018 11:24 ከሰዓት
Last updated
April 16, 2026 23:24
Weather
addis ababa 🌦 +17°C
ዜና

ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እንደ ከተማ በርካታ ውጤታማ ማሳያዎች ተተግብረዋል፡- ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር

08 ሚያዝያ 2018

ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እንደ ከተማ በርካታ ውጤታማ ማሳያዎች ተተግብረዋል፡- ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር
ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እንደ ከተማ በርካታ ውጤታማ ማሳያዎች ተተግብረዋል፡- ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እንደ ከተማ በርካታ ውጤታማ ማሳያዎች ተተግብረዋል፡- ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እንደ ከተማ በርካታ ውጤታማ ማሳያዎች ተተግብረዋል፡- ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እንደ ከተማ በርካታ ውጤታማ ማሳያዎች ተተግብረዋል፡- ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር

ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፤ መጋቢት 30 ቀን 2018 .

የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አዳጊ የሆነውን የተገልጋይ ፍላጎት ለማሟላት አገልግሎት አሰጣጣቸውን በማዘመን በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መፈጸም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መሰረት ያደረገ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የሰነዱ ዋና ዓላማ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመለየት ለመፍታት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገልጋዩ ማህበረሰብ እና የአገልግሎት አቅራቢው ተቋም መብትና ግዴታ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው ባለው የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው እንዲሻሻል በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ ነዉ።

ሰነዱን ያቀረቡት በቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ፍቅሬ ለአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻርና የአገልግሎት ሰጪውና ተቀባዩ መብትና ግዴታዎች ላይ ዝርዝር ማብራርያ ሰጥተዋል።

በተያያዘም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቢሮው ኃላፊ ክቡር / ጀማሉ ጀንበር እንደተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳዲስ ስትራቴጂዎችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ያሉ ሲሆን ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚደረጉ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እንደ ከተማ በርካታ ውጤታማ ማሳያዎች ተተግብረዋል ለዚህም ማሳያ የአዲስ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት በስድትስት /ከተሞች ተተግብሮ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በተለይም ሰፊ የተገልጋይ እንግልት የሚበዛባቸውን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ወደ ሪፎርም እንዲገቡ በማድረግ የማሻሻያ ተግባራት በማከናወን ቀጣይነት ያለው ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው አገልጋዩ ሰራተኛ አገልግሎትን ሲሰጥ ስነምግባር በተላበስ መልኩ መብትና ግዴታውን አዉቆ የሚያገለግል ብቁ ሰራተኛ መሆን እንደሚገባን አመላክተዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ምላሽ በመስጠት የዉይይት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።