ዜና
የአዲስ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የአዳዲስ ቅርንጫፎች ግንባታ ሂደት ላይ ግምገማ ተካሄደ
24 ታኅሣሥ 2018
የአዲስ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የአዳዲስ ቅርንጫፎች ግንባታ ሂደት ላይ ግምገማ ተካሄደ
የአዲስ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል ቅርንጫፎች መስሪያ ቤቶችን በሁሉም ክ/ከተማ ወደ ስራ ለማስገባት በተያዘው እቅድ መሰረት የግንባታ ሂደት እና የስራ እቅስቃሴን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ ግምገማ ተካሂዷል።
በመድረኩም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር እንደገለፁት የአዲስ መሶብ አዳዲስ ቅርንጫፎች የስራ ሂደት በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኝና ነገር ግን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ወጥነት ባለው መልኩ መሰራት እንዳለበት እንዲሁም ሁሉም በየ ድርሻው ትኩረት በመስጠት መተግበር እንዳለበት አቅጣጫ ሰጥተዋል።