Skip to content 
Location
Arada Subcity, woreda 06 Addis Ababa, Ethiopia
Date
ሰኞ, 19 ሚያዝያ 2018 12:56 ከሰዓት
Last updated
April 27, 2026 12:56
Weather
addis ababa: 🌦 +22°C
ዜና

ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ

18 ሚያዝያ 2018

ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ
ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል። እነዚህ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል።
‎ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ፣ የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል።